1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ አጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት በስፋት መሰራጨቱ

ዓርብ፣ ነሐሴ 22 2001

ከሐምሌ አጋማሽ አንስቶ በዋና ከተማ አዲስ አበባ እና በስድስት ክልሎች የተስፋፋው የአጣዳፊ ተቅማጥና ተውከት ስርጭት ሰሞኑን ተባብሶ በበሽታው የሚያዙት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዘግቧል ።

https://p.dw.com/p/JKt6
ምስል Daniel Pelz

ዛሬ በአዲስ አበባ ዋና ዋና ሆስፒታሎች የተዘዋወረው ዘጋቢያችን ታደሰ ዕንግዳው ሆስፒታሎች በታማሚዎች መጨናነቃቸውን አዳዲስ ታካሚዎችም ወደ ሆስፒታሎች እየጎረፉ መሆናቸውን ተመልክቷል ። እስካሁን የበሽታው ስርጭት መጨመሩ እና በበሽታው የሚያዙትም ቁጥር ከፍ ማለቱ ከመገለፁ በስተቀር ምን ያህል ሰዎች በበሽታው እንደሞቱ እና እንደተያዙ ከሚመለከተው ክፍል የተገኘ አሀዛዊ መረጃ የለም ።

ታደሰ ዕንግዳው፣ ሂሩት መለሰ