1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰብዓዊ መብቶች አቤቱታ

ዓርብ፣ ጳጉሜን 4 2008

15 የመብት ተሟጋቾችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔ ፤ በኢትዮጵያ መንግሥት እየተፈፀመ ያለዉን የመብት ጥሰት ትኩረት ሰጥቶ እንዲወያይበት ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/1JzSO
Belgien Wenig Touristen auf dem Grand Place in Brüssel
ምስል Getty Images/AFP/T. Monasse

[No title]

ድርጅቶቹ በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የተወሰደዉ የኃይል ርምጃ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ኮሚሽኑ ያቀረበዉን ጥያቄ በመደገፍ ዉሳኔ እንዲያሳለፍ ጥሪ አቅርበዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዛይድ ራድ አልሁሴን ቀደም ሲል፤ በቅርቡ ደግሞ የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየተፈፀመ ያለዉ ግድያ እንዲቆምና የተፈፀመዉ ግድያም በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጥሪ ቢያቀርቡም የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪዎቹን እንደማይቀበል አስታዉቋል። የብረስልሱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለዉ።


ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ