1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሥልጣን ሽግግር እንዴት?

ዓርብ፣ የካቲት 9 2010

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ላይ መቼ ውሳኔ እንደሚሰጥም ሆነ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መቼ እንደሚሰየም በግልጽ የተነገረ ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/2spIG
Hailemariam Desalegn
ምስል picture alliance/dpa/K. Fukuhara

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በገዛ ፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው እነሳለሁ ማለት እያነጋገረ በርካታ ጥያቄዎችንም እያስነሳ ነው። ለድርጅታቸው እና ለመንግሥት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ትናንት የተናገሩት አቶ ኃይለ ማርያም ጥያቄያቸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ በኃላፊነታቸው ላይ እንደሚቆዩ አሳውቀዋል። ሆኖም የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ላይ መቼ ውሳኔ እንደሚሰጥም ሆነ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መቼ እንደሚሰየም በግልጽ የተነገረ ነገር የለም። በኢትዮጵያ ብዙም ካልተለመደው ከአቶ ኃይለማርያም የሥልጣን መልቀቅ ጥያቄ በኋላ የሥልጣን ሽግግሩ እንዴት ሊሆን ይችላል? ምንስ ይጠበቃል? ስንል የሕግ ባለሞያ አቶ ተማም አባቡልጎን አነጋግረናል። የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ