1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የአጫሽ ቁጥርን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረት 

ሐሙስ፣ የካቲት 21 2011

ኢትዮጵያ በቅርቡ ያወጣችው የትምባሆ ቁጥጥር ሕግ ከ 90 ቀናት በኋላ በሲጋራ ፓኬቶች ላይ አስፈሪና አስደንጋጭ ምስሎችን በማተም፡ በነጠላ ፍሬ መሸጥን በመከልከል ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ተገለፀል፡፡

https://p.dw.com/p/3EGlP
Deutschland Bundeskabinett billigt Schockbilder auf Zigarettenpackungen
ምስል picture-alliance/dpa/J. Güttler

ሲጃራ


ኢትዮጵያ በቅርቡ ያወጣችው የትምባሆ ቁጥጥር ሕግ ከ 90 ቀናት በኋላ በሲጋራ ፓኬቶች ላይ አስፈሪና አስደንጋጭ ምስሎችን በማተም፡ በነጠላ ፍሬ መሸጥን በመከልከል ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ተገለፀል፡፡ ይሁንና ሕጉ አሁንም ከሲጋራ አምራች፡ አከፋፋይ እና ቸርቻሪ ድርጅቶች እክል እንዳይገጥመው ስጋት አጭሯል፡፡ የኢትዮጵያ ሥነ-ምግብ ኢንስቲቲዩት በቅርቡ በ 10 ከተሞች ላይ ባደረገው ጥናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኛው ለገበያ የሚቀርበው የሲጋራ ምርት በብሔራዊ ትምባሆ ድርጅት የሚመረቱት 5 የሲጋራ አይነቶች መሆናቸዉን አረጋግጦአል። በምስራቅ አፍሪቃ ቀዳሚ የሲጋራ አምራች መሆንን ርዕዩ አድርጉ የተነሳው ድርጅቱ በሌላ በኩል መንግስት የቁጥጥር ሕግ ማውጣቱ የሚጣረስ አካሄድ ነው  በሚል በብዙዎች ዘንድ ስጋትን አጭሯ። የጤና ልማት እና ፀረ- ወባ ማኅበር ያወጣው መረጃ እንደሚያመለክተዉ፤ በኢትዮጵያ 33.4 ሚሊዮን ሕዝብ ሲጋራ ያጨሳል፤ በሲጋራ ማጨስ ምክንያት ብቻ በየዓመቱ 17 ሽህ ሰዉ ይሞታል።   

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ