1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ፍላጎትና አቅርቦት

እሑድ፣ ኅዳር 1 2006

ኢትዮጵያ የተለያዩ የኃይል ምንጮችን ለኤሌክትሪክ አቅርቦት ለመጠቀም ጥረት ከተጀመረች ዓመታት አልፏታል።

https://p.dw.com/p/1AES8
ምስል Fotolia/Thorsten Schier

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ የዉሃ ሀብትን ለኤሌክትሪክ ማመንጫነት ለማዋል በየቦታዉ ከተጀመሩት እንቅስቃሴዎች ባሻገር፤ የንፋስ እና ፀሐይ ኃይል እንዲሁም የከርሰ ምድር እንፋሎትን ለኤሌክትሪክ ምንጭነት ሥራ ላይ ማዋል መጀመሩ ሀገሪቱ በዘርፉ በቂ አቅርቦት እንዲኖራት እንደሚያስችል ይታመናል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንም የአቅርቦት እጥረት የለም ባይ ሲሆን ፤ ለጎረቤት ሀገር ማለትም ለጅቡቲ ሽያጭ መጀመሩ ተገልጿል። ድርጅቱ እንደሚለዉ የሚሸጠዉ ከሀገር ዉስጥ ፍጆታ ሲተርፍ ብቻ ነዉ። በተቃራኒዉ የሀገር ዉስጥ ደንበኞቹ ኤሌክትሪክ እንደሚቆራረጥ፤ ዋና ከተማ አዲስ አበባን ጨምሮ፤ ሰዓታት ቀርተዉ ለቀናትም እንደሚጠፋባቸዉ ይናገራሉ። አቅም እያለ ለምን ይቋረጣል? ዶይቼ ቬለ ባለሙያዎችን ጋብዞ ያወያየበት ርዕሰ ጉዳይ ነዉ። ዝርዝሩን ከድምፁ መረጃ ያድምጡ!

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ