በኢትዮጵያ ይካሄዳል የተባለው የስልክና የኢንተርኔት ጠለፋ
እሑድ፣ ሚያዝያ 5 2006ማስታወቂያ
ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት HRW በኢትዮጵያ የስልክና የኢንተርኔት ስለላ ይካሄዳል ሲል በቅርቡ ባወጣው ዘገባ አጋልጧል ። HRW በዚሁ የጥናት ውጤት መንግሥት የሚቆጣጠረውን የቴሌኮምኒኬሽን መስሪያ ቤትና አገልግሎት የግለሰቦችን ሚሥጥር የመጠበቅን ፣ ሃሳብን በነፃ የመግለፅና የመደራጀትን እንዲሁም መረጃ የማግኘት መብትን ለመገደብ እየተጠቀመበት ነው ሲልም አስታውቋል ። ድርጅቱ በመንግሥት ይፈፀማል ካለው ስለላ ሰለባዎች መካከልም ተቃዋሚዎች ጋዜጠኞች እንዲሁም ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴ አካሂዳችኋል ተብለው የታሰሩ ሰዎች ይገኙበታል ። መንግሥት ግን ለአንዳንድ የዜና ወኪሎች በሰጠው ምላሽ ዘገባውን አስተባብሏል ።በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ በኢትዮጵያ ይካሄዳል የተባለውን የስልክና የኢንተርኔት ጠለፋ እንዲሁም በሃገሪቱ የግለሰቦችን ሚስጥር የመጠበቅና መረጃ የማግኘት መብት ይዞታን ይዳስሳል ። በውይይቱ የተካፈሉት ተሳታፊዎች ከሰነዘሩዋቸው ሃሳቦች የሚከተሉት ይገኙበታል ።
ሂሩት መለሰ
ልደት አበበ