1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ድርቅና ተፅእኖዎቹ

እሑድ፣ ነሐሴ 17 2007

በድርቁ ምክንያት በቆላማ አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የቀንድ ከብቶች ሞተዋል ። የዝናብ እጥረት ባስከተለው ድርቅ መንስኤ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥርም ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ ሆኖ መገኘቱ ተነግሯል ።

https://p.dw.com/p/1GJcO
Dürre – Äthiopien
ምስል European Commission DG ECHO / CC BY-SA 2.0

በኢትዮጵያ ድርቅና ተፅእኖዎቹ

በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩት በ2007 ዓም የበልግ እንዲሁም የክረምቱ ዝናብ መዘግየቱና በበቂ መጠን አለመጣሉ የሰብል ምርት ላይ ተፅእኖ አሳድሯል ። የችግሩ ሰለባ የሆኑትም በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ፣ በሰሜን ምሥራቅ አማራ ክልል ፣ በደቡባዊ ትግራይ በአፋር እና በማዕከላዊና ምስራቅ ኦሮምያ ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎች መሆናቸው ተገልጿል ። በድርቁ ምክንያት በቆላማ አካባቢዎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የቀንድ ከብቶች ሞተዋል ። የዝናብ እጥረት ባስከተለው ድርቅ ምክንያት የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥርም ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ ሆኖ መገኘቱ ተነግሯል ።በመጢው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ በኢትዮጵያ ድርቅና ተፅእኖዎቹ ላይ ያተኩራል ። በውይይቱ ከተነሱት ሃሳቦች የሚከተሉት ይገኙበታል ።

ሒሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ