1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭት፣ተቃውሞ እና የመንግስት እርምጃዎች

እሑድ፣ ጥር 27 2010

በኢትዮጵያ እሥረኞች መፈታት ከጀመሩ በኋላ ተቃውሞ እና ግጭት ጋብ ያለ መስሎ ነበር ።ሆኖም ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በተለይ ሰሜን ወሎ ውስጥ በተለያዩ ከተሞች የተነሳው ግጭት አሁንም አለመርገቡ ነው የሚሰማው።

https://p.dw.com/p/2s3Dl
Karte Äthiopien englisch

ውይይት፦ ግጭት ተቃውሞና የመንግስት ርምጃዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ  «የተሻለ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት» በሚል ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት በፌደራል እና በክልል ተይዘው የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ እሥረኞች ተለቀዋል። እየተለቀቁም ነው። ሆኖም እርምጃው በዜጎችም በውጭ መንግሥታትም ተወድሶ ሳያበቃ፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነጻጸር አንጻራዊ ሰላም ነበረው በሚባለው በሰሜን ወሎ ወልድያ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ አጎራባች ከተሞች ተዛምቶ የሰዎች ህይወት አልፏል፣ንብረት ወድሟል፤ በርካቶችም ታስረዋል።  የአማራ ክልል ችግሩን ለመፍታት ከወጣቶች ጋር መነጋገሩን ቢያሳውቅም ግጭቱ አለመርገቡን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እስከዚህ ሳምንት አጋማሽ ድረስ ሲዘግቡ ነበር። በግጭቱ በአካባቢው ከተሞች የንግድ የትራንስንስፓርት እና የሥራ እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል። በኢትዮጵያ የቀጠለው ተቃውሞ እና ግጭት እንዲሁም የመንግስት እና የክልሎች ርምጃዎች የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው። 

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ