1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጽያ በተ.መ የአለም የምግብ ፕሮግራም ሰራተኞች ላይ የደረሰ ጥቃት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2003

የተባበሩት መንግስት የአለም የምግብ ድርጅት ባለፈዉ አርብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰራተኞቹ ላይ ጥቃት መድረሱን አስታወቀ ።

https://p.dw.com/p/ROR6
ድሪደዋምስል DW

አደጋው ባልታወቁ ታጣቂዎች መጣሉን የሚገልጸዉ የአለም የምግብ ድርጅት በጥቃቱ አንድ ሰዉ መሞቱን እንዲሁም አንድ መቁሰሉን ሌሎች ሁለት ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ ገልጿል ። ሰራተኞቹ ጥቃቱ የተጣለባቸው ከጅጅጋ ተነስተው ጉለልቼ ወደተባለች ቀበሌ ሲጓዙ ነበር ። በአለም የምግብ ድርጅት ሰራተኞች ላይ በሶማሌ ክልል በፊቅ ዞን ስለደረሰዉ አደጋ የድሪደዋዉ ወኪላችን ዪሃንስ ገብረግዚአብሄር ዘገባ ልኮልናል

ዮሃንስ ገብረግዚአብሄር

አዜብ ታደሰ