በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ጉዳይ የመኢአድ ተቃውሞ 

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:54 ደቂቃ
12.06.2018

«የገዥዉን ፓርቲ ዉሳኔ አጥብቀን እንቃወማለን»

በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ጉዳይ የመኢአድ ተቃውሞ ባወጣዉ መግለጫ የኢትዮጵያን መሪት ቆርሶ ለመስጠት የሚደረግ ጥረት ሁሉ እንዲቆም፤ አጥብቀንም እንቃወማለን ሲል አስታወቀ።

 
መላው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ በምህጻሩ፣ መኢአድ፣  የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት እና በአልጀርሱ ሥምምነት መሠረት የተሰየመዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ዉሳኔን ገቢራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት «ያለማመንታት በቁርጠኝነት» የሚሰራ መሆኑን መግለፁ ተቃወመ።  መኢአድ ዛሬ በጽ/ቤቱ ባወጣዉ መግለጫ የኢትዮጵያን መሪት ቆርሶ ለመስጠት የሚደረግ ጥረት ሁሉ እንዲቆም፤ አጥብቀን እንቃወማለን ሲል በመግለጫዉ አስታዉቋል።  


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ