1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢንተርኔት የታገዘ ትምህርት በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ መስከረም 30 2005

በቅርቡ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በተካሄደው በጀርመን የኢትዮጵያ ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የሚታየውን የሰው እጥረት ችግር E-LEARNINGን ስላለው ሚና ውይይት ተካሂዷል።

https://p.dw.com/p/16NYr
BrightSpark Education offers long-distance tutoring via the internet. This young UK company outsources math tuition for 7-16 year-olds to graduates recruited and trained in India. Source: Nina Potts
ምስል DW/Potts

በጀርመን የኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር የተቋቋመው እአአ በ 2009 ዓ, ም ነው። የማሕበሩ አላማ በጀርምን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በትምህርት ዘርፍ የሚያደርጉትን ጥረት ማበረታታትና በተማሪዎችና በትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን መደገፍ ነው። ማህበሩ በቅርቡ በፍራንክፈርት ከተማ አንድ ስበሰባ አድርጓል። በስብሰባው ላይ በኢንተርኔት የታጋዘ ትምህርት ወይ በኢንግሊዘኛው E-LEARNING፣ በኢትዮጵያ እውቀትን የማስፋፋት ሂደት ውስጥ ስለሚጫወተው ሚና ፣ የፀሐይ ኃይልን በመጠቀም የኤሌክትርክ ኃይል ለገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ስለማድረስና ኢትዮጵያ በሌላው ዓለም ዘንድ ያላትን ገጽታ በተመለከተ ከባለሙያዎቹ ጋር ምክክርና ውይይት ተደርጓል። ለዛሬው በሳይንስና ህብረተሰብ ዝግጅት የምናቀርበው በኢትዮጵያ በኢንተርኔት ታግዞ ስለሚሰጥ ትምህርት ነው።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Hauptcampus der Universität Addis Abeba (AAU) Thema: Die Universität Addis Abeba (AAU) ist traditionell ein Hort der politischen Opposition. Die Proteste gegen die Wahlfälschungen 2005 wurden nicht zuletzt von Studenten auf die Straße getragen. Sicherheitskräfte patroullieren derzeit verstärkt auf dem Campus Schlagwörter: Universität Addis Abeba, University of Addis Ababa (AAU), Proteste 2005, Wahl Äthiopien 2010, Ethiopia 2010
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ለሌሎች የኢትዮጵያ ዮንቨርስቲዎች የኢ ለርኒንግ ማዕከል ለመሆን አቅዷል።ምስል DW

በኢንተርኔት የታገዘ ትምህርት ወይም E-LEARNING በየትኛውም ሰዓት ከየትኛውም ቦታ መረጃና እውቀትን ለመቀበልና ለማስተላፍ የሚያገለግል የትምህርት ዘዴ ነው።

በቅርቡ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በተካሄደው በጀርመን የኢትዮጵያ ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የሚታየውን የሰው እጥረት ችግር E-LEARNINGን ስላለው ሚና ውይይት ተካሂዷል። በማህበሩ ስብሰባ ላይ ከተገኙት ውስጥ አንዱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ይህ የትምህርት ዘዴ ወደ ፊት በኢትዮጵያ በተለይም በከፍተኛ ተቋም አሰራር መጫወት ስለሚችለው ሚና ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ኃይላቸውን በስደት ምክንያት በማጣት ከሚታወቁ ሀገራት ግንባር ቀደሟ ናት። 75 በመቶ የሚሆኑ የተማሩ ዜጎቿ ሌላ ሀገር ውስጥ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ይኖራሉ። ይህ አሳሳቢው የተማረ ሰው ስደት በርካታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖሊቲካዊ ምክንያቶች እንዳሉት የሚገልጹ ብዙዎች ናቸው።

GettyImages 74584876. BEKOJI, ETHIOPIA - MAY 17: Schoolchildren in class at the famous Bekoji school where many top runners were educated on May 17, 2007 in Bekoji, Ethiopia (Photo by Gary M. Prior/Getty Images).
የአንደኛ ደረጓ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአርሲ-በቆጂ። የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።ምስል Getty Images

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ዩኒቨርስቲና ኮሌጅ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቁጥር ወደ 31 መጨመሩ በየዓመቱ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተማሩ ተማሪዎች ቁጥር እንዲጨምር አንዱ ምክንያት ነው። በዚህም ላይ በተለያዩ ያገሪቷ ግዛቶች ከትምህርት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ወደ ፊት ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ መረጃዎች ያመለክታሉ። ነገር ግን የከፍተኛ ተቋማት ቁጥር እድገትና የትምህርት ጥራት እድገት እኩል ትኩረት የተሰጣቸው አይመስሉም። ብዙዎች የኢትዮጵያ መንግስት ለትምህርት ጥራት የሰጠው ቦታ ትንሽ ነው ሲሉ፣ መንግስት በበኩሉ ለትምህርት ተደራሽነት ቅድሚያ ሲሰጥ የጥራት ጉዳይ በሂደት ይፈታል የሚል ተስፋ እንዳለው ነው የሚገለጸው።

Logo des Deutsch-Äthiopischen Studenten- und Akademikervereins e.V. (DÄSAV e.V.) *** Nur für die Berichterstattung über die Äthiopien-Tagung "Äthiopien zwischen Gestern und Heute" zu nutzen // Eskinder Mamo ***

ኢትዮጵያ ውስጥ በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ ትምህርት መስጠት ከተጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል። ለምሳሌ የሁለተኛ ደረጃ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን የፕላዝማ ቴሌቪዥን ትምህርት ማዳረስ በሚል ዓላማ መንግስት ከበጀቱ 10 በመቶውን ለዚሁ ጉዳይ አውሎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ቢሆንም ይህ ዘዴ ብዙ ማህበራዊ ጉዳዮችን ከግምት ባለመስገባት የተጀመረ ስለ ነበረ በትምህርት ጥራት ላይ ያመጣው ለውጥ የታሰበውን ያክል እንዳልሆነ ነው የሚታየው። ከፍተኛ ተቋማትን በኤሌክትሮኒክስ በታገዘ ዘዴ በማገናኘት መረጃና እውቀትን ለማሰራጨት የታሰበው ስራ ከአፍሪቃ በኢንተርኔት አቅርቦቷ ዝቅተና ከሆነችው ኢትዮጵያ እንዴት ሊሰራ ይችላል? ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልፀውልናል።

እንዲህ ዓይነቱ በኢንተርኔት የታገዘ በከፍተኛ ተቋማት መካከል ሊደረግ የሚችለው የመረጃ ልውውጥ ተግዳሮት የሚሆን በቂ የእንተርኔት መረብ አለመኖር ብቻ አይደለም። በከፍተኛ ተቋማት እንዲህ ያለውን የእውቀት ልውውጥ ለማበረታት የተማረ ሰው ኃይል እጥረት፣ የፖሊሲዎች አለመኖርና፣ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች አለመገንባትና የገንዘብ እጥረት ዋነኞቹ እንቅፋቶች ናቸው።

ደክተር ጌታሁን የዘረዘሯቸውን ችግሮች ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት በጀርመንም ሆነ በሌሎች የውጭ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ምን ማድረግ ይችላሉ? በጀርመን የኢትጵያውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር ሊቀ መንበር የሆኑት አቶ ኤስክንድር ማሞ ማሕበሩ፣ እውቀትና ችሎታ ያላቸውን ሰዎችና እርዳታ የሚሰጡ ተቋማትን ማፈላለግ ላይ እንዲሁም አስፈላጊውን ገንዘብ ማግኘቱ ላይ ትልቅ ሚና መጫወት እንደሚችል አመልክተዋል።

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ