1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በእስር ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች በይቅርታ ሊፈቱ ነው

ሰኞ፣ ጥር 7 2010

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እስከ መጪው ረቡዕ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በፌደራል ደረጃ ጉዳያቸው ከተያዘ ተጠርጣሪዎች ውስጥ 115 ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል፡፡ የይቅርታ ሂደቱ እስከሚቀጥለው ሁለት ወራት እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/2qsGf
PK von Äthiopiens Generalstaatsanwalt
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የይቅርታ ሂደቱ ሁለት ወር ይወስዳል ተብሏል

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ ኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት እነዚህን ጨምሮ በአጠቃላይ በእስር ላይ የሚገኙ 528 ተጠርጣሪዎች በይቅርታ ይፈታሉ ብለዋል፡፡ የመጀመሪያው ዙር የይቅርታ ሂደት እስከሚቀጥለው ሁለት ወራት እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በክልሎች ጭምር ይቀጥላል በተባለው የይቅርታ እና ክስ የማቋረጥ ሂደት እስካሁን ተጠቃሚ የሆኑት በፌደራል ደረጃ እና በደቡብ ክልል ያሉ ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ የጠቅላይ አቃቤ ህጉን መግለጫ የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር የላከውን ዝርዝር ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ፡፡  

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

ተስፋለም ወልደየስ

አርያም ተክሌ