1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በካማሺ ዞን ቤንሻንጉል ጉሙዝ የቀጠለው የታጣቂዎች ጥቃት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 13 2013

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሰዳል ወረዳ ታጣቂዎች ፖሊሶችን ጨምሮ በንጹሐን ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ በርካቶችም ከመኖሪያ አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3sKhe
Äthiopien Vertreibung und Massaker in der Region West-Benishangul Gumuz
ምስል Maria Gerth-Niculescu/DW

ታጣቂዎቹ ግድያ ፈጽመው ቤቶችን አቃጥለዋል ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሰዳል ወረዳ ታጣቂዎች ፖሊሶችን ጨምሮ በንጹሐን ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ በወረዳው ከባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጀምሮ ታጠቂዎች በተለያዩ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ ጥቃት ማድረሳቸውን መጀመራቸውን ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡ ሰኞ ማታ በነበረው ጥቃት ደግሞ ከነዋሪዎች ከአራት በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉንና ቤቶችም መቃጠላቸውን ከጥቃት ሸሽተው ወደ መንዲ እና ዳላቲ የተባሉ አጎራባች አካባቢዎች የሸሹ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ነዋሪዎች ቀያአቸውን ለቀው ወደ ተለያዩ ከተሞች እየሸሹ መሆኑም አክለው ተገልጸዋል።  የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱላዚም መሐመድ በሰዳል ወረዳ ታጣቂዎች ጉዳት ማድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ