1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኬንያ የአዉቶቡስ ተጓዦች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 13 2007

ሰሜን- ምስራቅ ኬንያ ውስጥ የሶማሊያው ዓማጺ ቡድን አሸባብ አውቶቡስ ውስጥ የነበሩ 28 ሰዎች መግደሉን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1Drcu
Bus, Nairobi, Kenia
ምስል picture-alliance/dpa

አማጺ ቡድኑ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኝ « ማንዴራ » በተባለች ከተማ የአውቶቡስ ተሳፋሪዎችን በማስቆም፤ ቅዱስ ቁራን ማንበብ የማይችሉትን በሙሉ በጥይት ተኩሶ መግደሉ ተገልጿል። ሟቾቹ በሙሉ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ አልነበሩም። አሸባብ በተተደጋጋሚ ኬንያ ውስጥ ጥቃት መጣሉ ይታወቃል። ቡድኑ እኢአ 2013 ዓም መዲና ናይሮቢ በሚገኝ አንድ የገበያ አዳራሽ ውስጥ በጣለው ጥቃት ቢያንስ 67 ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁ ባለፈው ሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የባህር ዳርጃ አካባቢ ባደረሰው ጥቃት 60 የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል። አሸባብ በተደጋጋሚ ኬንያ ላይ ጥቃት ያደረሰው ፤ የኬንያ ዓለም አቀፍ የጦር ወታደሮች አማፂ ቡድኑን ለማዳከም እና በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር ወደ ሀገሪቱ በመዝመታቸው ነው። በዚህም የተነሳ ቡድኑ በተደጋጋሚ የበቀል ጥቃት እያደረሰ ይገኛል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ