1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወሎ ማጅራት ገትር መሰል በሽታ የሰው ህይወት ማጥፋቱ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 21 2001

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ቃሎ ወረዳ ተከስቶ ምንነቱ በውል ባልታወቀ ማጅራት ገትር መሰል በሽታ ሀያ ሰዎች መሞታቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/IyqK
ምስል DW-TV

ሚንስቴሩ እንዳስረዳው፡ በሶስት ቀበሌዎች የተከሰተው ይኸው ወረርስኝ ወደሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋ ግብረ ኃይል አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ ነው። የተመድ የሰብዓዊ ርዳታ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት፡ በምህጻሩ ኦቻም ወረርሽኙ ከታየባቸው አካባቢዎች የተወሰደው ናሙና በሽታው በርግት ማጅራት ገትር መሆን አለመሆኑ እየተመረመረ መሆኑን አመልክቶዋል።

ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ