1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወግ ያልተያዘዉ ሀብት

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2005

ዉሃ ጥንቃቄ ከማይደረግላቸዉ የተፈጥሮ ሃብቶች አንዱና ዋነኛዉ ነዉ። ከቤት ዉስጥ አገልግሎት አንስቶ ለእርሻዉና ለኢንዱስትሪዉ ፍጆታ ያለእቅድ ሥራ ላይ የሚዉለዉ ዉሃ ተገቢዉ ጥንቃቄ ካልተደረገለት ቀስ በቀስ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል የዘርፉ ተመራማሪዎች ጥናት ዉጤት ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/17YW1
ምስል JENNY VAUGHAN/AFP/GettyImages

ከተፈጥሮና የአጠቃቀም ጉድለት ተዳምሮም ሐይቆችና ወንዞችን ማድረቅ መጀመሩም የዚህ ማስጠንቀቂያ ነዉ የሚሉ አሉ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ወንዞች እና ሃይቆች ዉሃቸዉ ነጥፎ እየደረቁ ነዉ። ሰባት ቢሊዮን ለደረሰዉ የዓለም ህዝብ መሠረታዊ የሆነዉ ህይወት አለምላሚ ዉሃ ከየምንጩ በሚያርፍበት ከፍተኛ የተፈጥሮና ሰዉ ሠራሽ ምክንያት ለችግር መጋለጡ ይታያል።

Wasser Trinkwasser Wasserhahn läuft
ምስል Fotolia/Dev

ዉሃ ለመጠጥ፤ እህል ለማምረት፤ ምግብ ለማብሰል፤ ለኃይል ምንጭነት እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ምርትና ለመሳሰሉት በከፍተኛ ደረጃ ሥራ ላይ ይዉላል። በየቀኑ ለእርሻ፤ ለኢንዱስትራና ለንግዱ ዘርፍ የሚዉለዉ ሳይጠቀስ አራት የቤተሰብ አባላት በአንድ ቤት ብቻ በአማካኝ ወደ400 ጋሎን ዉሃ ይጠቀማሉ ተብሎ ይገመታል። የዉሃዉ ምንጭ ጥንቃቄ ስለማይደረግለትም ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገሮች የዉሃ አካላት መድረቃቸዉ እየታየ ነዉ። ጥናቶች ከወዲሁ እንደሚያመለክቱት እንደልብ ያለዋጋ በየወንዙና ባህሩ የሚፈሰዉ ዉሃ ከዓመታት በኋላ እንደተፈለገ ሊገኙ ከማይችሉ የተፈጥሮ ሃብቶች ተርታ ሊገባ እንደሚችል ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ