1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዉጭ የሚገኙ የኢትዮጵያን ቅርሶች ለማስመለስ ጥረት

ሰኞ፣ ኅዳር 6 2008

የብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ በተለያዩ መንገዶች ከሀገር የወጡ በርካታ ቅርሶችን እንዲመለሱ ለማድረግ ምሁራንና ባለሞያዎችን አወያየ።

https://p.dw.com/p/1H5GX
Frankreich Äthiopien christliche und islamische Schriften in Paris
ምስል DW/Haimanot Turuneh

በመክፈቻዉ ሥነ-ስርዓት ላይ የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርኃም ጦሳ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ንግግር አድርገዋል። ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ዘመንዋ ያሰባሰበችዉ የማንነትዋ መለያ የሆኑ በዉቅ የተሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ብርቅዬ ቅርሳ ቅርሶችዋ በተለያዩ ጊዚያት ከሀገር የወጡ በመሆናቸዉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰም ተመልክቶአል። አሁንም በሀገሪቱ ዉስጥ የሚገኙት ጥንታዊ ቅርሶች በሕገ-ወጥ እጅ ገብተዉ በተለያዩ መንገዶች ወደ ዉጭ ሃገራት እንዳይወጡ፤ ለሽያጭ እንዳይዉሉ መንግስት ቁጥጥር ማድረግ እንዳለበት ተመልክቶአል ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ፤ ባለሞያዎችንና ያገባናል ያሉ አንዳንድ ሰዎችን አነጋግሮ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ