1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በውጭ የሚገኙ 24 የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ማሳሰቢያ

ሰኞ፣ የካቲት 21 2014

የዐማራ ቅርስ ያሏቸው አካባቢዎችን ለድርድር ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ተቃወሙ።

https://p.dw.com/p/47iFH
Karte Äthiopien englisch

በውጭ የሚገኙ 24 የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ማሳሰቢያ

የዐማራ ቅርስ ያሏቸው አካባቢዎችን ለድርድር ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ተቃወሙ። የማኀበረሰብና የሚዲያ 24 ድርጅቶች ያወጡትን መግለጫ አስመልክቶ ተወካያቸው ኢንጂነር ሕዝቅኤል እስክንድር ለዶይቸ ቨለ፣ ወልቃይት፣ ራያና አካባቢው ከሕገ መንግሥት ዕውቅና ውጭ በህወሓት ተወስደው የነበሩ መሬቶች ሲሆኑ  ለድርድር ከቶውንም ሊቀርቡ አይችሉም ሲሉ ገልጸዋል።

የትግራይ ክልልን በመወከል በውጭ የሚንቀሳቀሰው ኮሚቴ አባልና የቀድሞ ዲኘሎማት ዮሐንስ አብርሃ በበኩላቸው፣ የይገባኛል ጥያቄ የተነሳባቸው ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ከ30 በላይ የትግራይ ቀበሌዎች ዐማራ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የመንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ ጉዳዩን አስመልክቶ ዶይቸ ቨለ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ የተጠቀሱትን አካባቢዎች በተመለከተ መንግሥት የሚያካሄደው ድርድር እንደሌለ አስታውቀዋል።

ታሪኩ ኃይሉ 

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ