1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዐረብ ሀገሮች ያሉ ኢትዮጵያውያን ችግር

ቅዳሜ፣ መጋቢት 8 1999

በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በዐረብ ሀገሮች በሥራው ዓለም ተሠማርተው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ብዙ ችግር ያጋጥማችዋል። ይህንኑ በተመለከተ ባልደረባዬ ሀብቶም ተክሌ እና እኔ አርያም ተክሌ ባንድነት ከራሳቸው ከሰለባዎቹ፡ የነርሱን ችግር ለማቃለል ከሚሞክሩ ድርጅቶችና በሳውዲ ዐረቢያ ከሚገኙት የኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደናል። ----------ይዞራል

https://p.dw.com/p/E0Xb
በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙት ዐረባውያት ሀገሮች ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በሥራ ላይ ተሠማርተው ኑሮአቸውን በመምራት ላይ ይገኛሉ። ከነዚሁ መካከል ብዙዎቹ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥረው የሚሠሩ ሴቶች ሲሆኑ ከአሠሪዎቻቸው ብርቱ በደልና ሥቃይ እንደሚደርስባቸው፡ እንዲሁም፡ አንዳንዶቹ በትንንሽ ወንጀል በየወህኒ ቤቶች ውስት ኢሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ራሳቸው ሰለባዎቹ እና ለሰብዓዊ መብት የሚሟገቱ ድርጅቶች በየጊዜው ከሚያወጡዋቸው ዘገባዎች ለመረዳት ተችሎዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ከተጎጂዎቹ፡ ችግራቸውን ለማቃለል ከሚሞክረው አዲስ አበባ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የማይግሬሽን መሥሪያ ቤት የሕገ ወጥ ፍልሰት ቢሮ ባለሥልጣን ወይዘሮ አሰፋች ኃይለሥላሤ፡ ከኢትዮጵያ የሠራተኞችና ማኅበራዊ መሥሪያ ቤት የሰው ኃይል ጥናትና ስታትስቲክስ ቡድን የሥራ ፈቃድ ሰጪ ክፍል ተወካይ ከአቶ ሳውድ መሀመድ፡ ከዐረብ ሀገሮች የተመለሱ ሰለባዎች ከመሠረቱት የጎመና ኢትዮጵያ ማኅበር ኃላፊ ከአቶ ዮናስ ታደሰ፡ እንዲሁም፡ በሳውዲ ዐረቢያ ጂዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንሲላ ጀነራል አምባሳደር አቶ ተክለአብ ከበደ ጋር የተካሄደው ውይይት እንደሚከተለው ይደመጣል።