በየመን የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ስቃይ
ሐሙስ፣ ጥር 8 2006ማስታወቂያ
ሳውዲ አረቢያ ህገ ወጥ የምትላቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎችን ብታባርርም አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን በየመን አቋርጠው ወደ ሃብታም የአረብ ሃገራት መጓዛቸው አላቋረጠም ። የሰነ የመን ዘጋቢያችን ግሩም ተክለ ሃይማኖት እንደዘገበው በየቀኑ ኢትዮጵያውያን ከ 3 እስከ 4 በሚደርሱ ጀልባዎች የመን እየገቡ ነው ። እነዚሁ የመን የደረሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለእንግልት ና ለልዩ ልዩ ስቃይ መዳረጋቸውን ዘጋቢያችን አስታውቋል ። ከሳውዲ አረቢያ ተባረው የመን የገቡ በርካታ ኢትዮጵያውያንም የከፋ ችግር ውስጥ እንደወደቁ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ነጋሽ መሃመድ ግሩምንና ሁለት የመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በስልክ አነጋግሯል ።
ግሩም ተክለ ሃይማኖት
ነጋሽ መሃመድ