በይርጋ ጨፌ ፤ የአርሶ አደሮች የመፈናቀል ሥጋት 3 ኅዳር 2007ረቡዕ፣ ኅዳር 3 2007በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴዖ አካባቢ የይርጋ ጨፌ ወረዳ ኑዋሪዎች የሆኑ ወደ 400 የሚጠጉ አባዎራዎች፤ ከመሬታችን የመፈናቀል ብርቱ ሥጋት አድሮብናል አሉ። አርሶ አደሮቹ፤ ለጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት ባቀረቡት የአቤቱታ ማመልከቻና ለ DW በሰጡት መግለጫ፣https://p.dw.com/p/1Dlz0ምስል DW/A. Hahnማስታወቂያ በከተማ መስፋፋት ስም ከመሬታችን ልንነቀል ነው ብለዋል። የይርጋ ጨፌ ከተማ ከንቲባ ግን እስካሁን መሬቱን ወደከተማ የማካለል ሥራ ተሠራ እንጂ ፣ አንድም ገበሬ ከመሬቱ አልተፈናቀለም ፣ ወደፊት የሚነሱበት ሁኔታ ሲፈጠር ግን፣ ተገቢው ካሣ ይከፈላቸዋል ማለታቸው ተጠቅሷል። ዝርዝሩን ---ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ተክሌ የኋላ ነጋሽ መሐመድ