1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ የተያዙት 24 ኢትዮጵያውያን

ሰኞ፣ ነሐሴ 5 2006

ባለፈው ሳምንት 24 ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ 16 ሰዎችን በምትጭን አንዲት ታክሲ ውስጥ ተሳፍረው ሲጓዙ የትራፊክ ፖሊስ እንዳስቆማቸው እና በብሪክስተን የፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተሰምቷል።

https://p.dw.com/p/1Cse0
Markt in Daveyton Südafrika
ምስል Gilberto Fontes

ከነዚህ ኢትዮጲያውያን መካከል የተወሰኑት ለአካለ መጠን ያልደረሱ መሆናቸውም ነው የተነገረው። በደቡብ አፍሪቃ ጁሀንስበርግ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ ስላስቆመው አንድ ታክሲ እና በውስጡም ተሳፍረው ስለነበሩት 24 ኢትዮጵያንን ጉዳይ ለማጣራት በቅድሚያ የሞከርነው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ወደተነገረበት የብሪክስተን ፖሊስ ነበር። ከፖሊስ ጣቢያው ግን የተገኘው መረጃ ኢትዮጵያኑ «»እንዴላ» ወደተባለ ጣቢያ መወሰዳቸውን ብቻ ነው። ለበለጠ መረጃ የጣቢያው አዛዥ ለቃለ መጠይቅ ፍቃደኛ አልነበሩም።

እንዲሁ በደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚመለከታቸው ሰው ለስራ ከቢሮ ውጪ እንደሚገኙ ተነግሮን ኢትዮጵያኑ በአሁኑ ሰዓት ስለሚገኙበት ሁኔታ ከነዚህ አካላት ለማወቅ አልተቻለም።ነገር ግን በደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ዋና ፀሀፊ አቶ ደረጀ መኮንን የሚያውቁትን ለዶይቸ ቬለ አካፍለዋል። ከዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ