1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ክልል የዱር አእዋፋት ላይ ወረርሽኝ ተከሰተ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 12 2011

ባለሙያዎቹ እንዳሉት ወረርሽኙ ባለፈው የመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሐመር ወረዳ ዘመርጋ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ከተከሰተ በኃላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ አጎራባች ቀበሌዎችና ወረዳዎች እየተዛመተ ይገኛል። 

https://p.dw.com/p/3H8Q4
Mauersegler
ምስል picture alliance/WILDLIFE

በደቡብ ክልል የዱር አእዋፋት ላይ ወረርሽኝ ተከሰተ

እዋፋትን የሚያጠቃው ወረርሽኝ የተከሰተው በክልሉ ድቡብ ኦሞ ዞን ሐመር እና በናደማይ በተባሉ ወረዳዎች ውስጥ መሆኑን በክልሉ የደበብ ኦሞ ዞን የእንሣትና አሳ ሀብት ልማት መምሪያ አስታቋል። ወረርሽኙ ባለፈው የመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሐመር ወረዳ ዘመርጋ በተባለ ቀበሌ ውስጥ ከተከሰተ በኃላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ አጎራባች ቀበሌዎችና ወረዳዎች መዛመቱን በመምሪያው የእንስሳት ጤና አጠባበቅ የስራ ሂደት አስተባባሪ ዶከተር ጎርባቾቭ ኩኒቴ ለዶቼ ቬለ (DW ) ገልደዋል። 

በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው በሽታ ከዚህ በፊት በአካባቢው ያልተለመደና አዲስ መሆኑን የጠቆሙት ዶከተር ጎርባቾቭ በተለይም በተለሞዶ ዋኔ በመባል የሚታወቁ የእርግብ ዝርያዎችን የማጥቃት አቅሙ የበረታ ሆኖ እንደሚስተዋል ተናግረዋል። 
በአሁኑ ወቅት የፌደራል ጤና ጥበቃና የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተቋቁሞ ወረሽኙ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የቅርብ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝና የሞቱ እእዋፋት ናሙናዎች በአዲስ አበባ ሰበታ በሚገኘው የእንስሳ ጤና ምርምር ላብራቶር ተልከው ውጤቱ እየተጠበቀ ይገኛል ብለዋል። 

የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የበሽታዎች መከላከልና ጤና ማጎልበት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ታምራት አሰፋ በበኩላቸው በወንዝ ዳርቻዎችና ኩሬዎች አካባቢ በወረርሽኙ ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ እእዋፋት ሞተው ቢገኙም አስከአሁን ግን በሰዎች ላይ የተከሰተ ተመሳሳይ ምልክት አለመኖሩን ተናግረዋል። 

ይሁን እንጂ ወረርሽኙ ምናልባት ወደ ሰዎች የመተላለፍ ሁኔታውን ለመቆጣጣር በሁለቱም ወረዳዎች በሚገኙ የጤና ተቋማት አማካኝነት የቅርብ ክትትልና ቅኝት እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ ታምራት ለዶቼ ቬለ (DW ) አስረድተዋል። በቀጣይ የናሙናው ውጢት እስኪታወቅ ድረስ ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛልም ብለዋል። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ልደት አበበ