1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው ቀውስ መባባሱ

ሰኞ፣ ኅዳር 1 2001

የአማፅያኑ መሪ ላውሬንት ንኩንዳ በበኩላቸው፤ ጦር ልኬ እዋጋለሁ ብሎ የደፈረ ሁሉ እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የሀፍረት ማቅ ይከናነባል ሲሉ ዝተዋል---

https://p.dw.com/p/Fqx2
ጄኔራል ሎራ ንኩንዳምስል picture-alliance/ dpa

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል፤ በመንግስት እንደሚደገፉ በሚነገርላቸው ሃይላትና አማፅያን መካከል ያገረሸው ብጥብጥ አዲስ አሰላለፍ መያዙ ተነገረ። የደቡብ አፍሪቃ አገራት በቦታው ሠላም አስከባሪ ሃይላት፣ ጎረቤት አገር አንጎላ ደግሞ ወታደሮቿን ለመላክ እንደተዘጋጁ ገልፀዋል። የአማፅያኑ መሪ ላውሬንት ንኩንዳ በበኩላቸው፤ ጦር ልኬ እዋጋለሁ ብሎ የደፈረ ሁሉ እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት የሀፍረት ማቅ ይከናነባል ሲሉ ዝተዋል። ዝርዝሩን ማንተጋፍቶት ስለሺ እንደሚከተለው አቀናብሮታል። ◄