1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠሩት ተበየነባቸዉ

ሐሙስ፣ የካቲት 18 2013

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈዉ ብይን መሠረት አንደኛዉ ተከሳሽ ጥላዬ ያሚ  በተከሰሰበት የወንጀል ጭብጥ ጥፋተኛ መሆኑ ተበይኖበታል

https://p.dw.com/p/3pw4Q
Äthiopien Hachalu Hundessa
ምስል Reuters/T. Negeri

በሐጫሉ ግድያ የተጠረጠሩ ተበየነባቸዉ

ኢትዮጵያዊዉን ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳን በመግደል፣ማስገደልና በአባሪ ተባባሪነት ከተጠረጠሩት 4 ተከሳሾች 3ቱ እንዲከላከሉ ተበየነባቸዉ።ዛሬ አዲስ አበባ ያስቻለዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባሳለፈዉ ብይን መሠረት አንደኛዉ ተከሳሽ ጥላዬ ያሚ  በተከሰሰበት የወንጀል ጭብጥ ጥፋተኛ መሆኑ ተበይኖበታል።በአባሪ ተባባሪነት የተጠረጠሩት ሁለተኛና ሶስተኛ ተከሳሾች ከዚሕ ቀደም የተጠቀሰባቸዉ የክስ አንቀፅ ተሻሽሎ በተለያዩ የሕግ አንቀፆች እንዲጠየቁ ችሎቱ በይኗል።አራተኛዋን ተከሳሽ ላምሮት ከማግል ግን በነፃ እንድትሰናበት ችሎቱ አዝዟል።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ