1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድሬደዋና ሐረር የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦአል 

ሰኞ፣ ሰኔ 10 2011

ከባለፈዉ ሰኞ ጀምሮ የአስረኛ እና የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና መጀመርን ተከትሎ በመላ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት እየተቆራረጠ የመረጃ ፍሰትና ስራን ማስተጓጎሎ ተገለፀ። በተለይ በምስራቅ  ኢትዮጵያ በድሬደዋና በሃረር ከተሞች የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና ከጀመረ ወዲህ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተነግሮአል።  

https://p.dw.com/p/3KauN
Afrika Pressefreiheit l Äthiopien - Internetcafé in Adama
ምስል Getty Images/AFP/S. Kolli

ከባለፈዉ ሰኞ ጀምሮ የአስረኛ እና የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና መጀመርን ተከትሎ በመላ ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት እየተቆራረጠ የመረጃ ፍሰትና ስራን ማስተጓጎሎ ተገለፀ። በተለይ በምስራቅ  ኢትዮጵያ በድሬደዋና በሐረር ከተሞች የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና ከጀመረ ወዲህ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተነግሮአል።  የኢንተርኔት አገልግሎት መስጫ መደብሮች ያልዋቸዉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት አገልግሎቱ በመቋረጡ ሥራቸዉም ተቋርጦአል። ነዋሪዎች የአስራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና ነገ ከተጠናቀቀ በኋላ አገልግሎቱ ዳግም ይለቀቃል የሚል ተስፋ መሰናቀጠዉን በድሬደዋ የሚገኘዉን ወኪላችን መሳይ ተክሌ ገልፆአልናል። መሳይን እዚህ ስቱዲዮ ከመግባቲ ከጥቂት ደቂቃ በፊት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ያሳደረዉን ተጽኖ እና ስለመቋረጡ ከሚመለከተዉ መሥራያ ቤት የተነገረ ነገር አለ? ስንል ጠይቀነዋል።

መሳይ ተክሌ

አዜብ ታደሰ  

እሸቴ በቀለ