1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድርቅ ለተጎዱት የኢትዮጵያዉያን ርዳታ

ዓርብ፣ መጋቢት 2 2008

ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ ወይም በእንግሊዝኛዉ ግሎባን አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ የተሰኘ በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የተቋቋመ ድርጅት ኢትዮጵያ ዉስጥ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 50ሺ የአሜሪካን ዶላር ርዳታ ሰጠ።

https://p.dw.com/p/1IBbi
Globale Allianz für Äthiopien in Nordamerika
ምስል DW/N. Wolde

[No title]

ድርጅቱ ከአባላቱ ያሰባሰበዉን ገንዘብ ለእርዳታ ፈላጊዎቹ ያደርስለት ዘንድ ዎርልድ ቪዥን የተባለዉን የእርዳታ ድርጅት መምረጡን አስታዉቋል። ድርጅቱ ሌሎች ኢትዮጵያዉያንም የፖለቲካም ሆነ የጎሳ ልዩነትን ወደጎን ብለዉ በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች እንዲደርሱ ጥሪዉን አቅርቧል። ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝሩል ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ