1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን ምርጫ የውጪ ዜጎች ተሳትፎ

ማክሰኞ፣ መስከረም 25 2014

ከሳምንት በፊት ጀርመን ባካሄደችው ሀገራዊ ምርጫ ከወትሮው የተለየ የመራጭ ሕዝብ ተሳትፎ እንደታየ ነው የሚነገረው። በዚህ ብሔራዊ ምርጫም ከ 500 በላይ ጀርመናዊ ዜግነት ያላቸው ከሌሎች ሃገራት ቤተሰቦች የተወለዱ ዕጩዎች በምርጫ ውድድሩ ተሳትፈዋል።

https://p.dw.com/p/41IdF
Bundestagswahl 2021 | Briefwahl Auszählung in München
ምስል Michaela Rehle/REUTERS

አውሮጳ፤ የጀርመን ምርጫና የውጭ ዜጎች

በአሁኑ ወቅት 83 ሚልዮን ከሚገመተው አጠቃላይ የጀርመን የሕዝብ ብዛት 21.3 ሚልዮኑ ወይም 26 በመቶ ያህሉ የውጭ ዜጋ መሠረት ያለውና በፍልሰት ወደ ሀገሪቱ የመጣ መሆኑን የጀርመን ስታትስቲክስ መሥሪያ ቤት መረጃ ያሳያል። ከወትሮው በተለየ ከፍተኛ መራጭ ሕዝብ በተመዘገበበት የዓለምን ትኩረት በሳበው የዘንድሮው የጀርመን ብሔራዊ ምርጫም ከ 500 በላይ ጀርመናዊ ዜግነት ያላቸው ከሌሎች ሃገራት ቤተሰቦች የተወለዱ ዕጩዎች በምርጫ ውድድሩ ተሳትፈዋል። ሆኖም ምን ያህሉ እንደተሳካላቸው ገና አልታወቀም። የስደተኞችን ጉዳይ በሚከታተለው ድርጅት ጥናት መሠረት እንደ ጎርጎሪዮስ የዘመን አቆጣጠር ከ 2013 እስከ 2017 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ከ 631 የፓርላማ ምክር ቤት አባላት 37ቱ ወይም 5.9 በመቶ ያህሉ ጀርመናዊ ዜግነትን የወሰዱ የውጭ ሀገር ዝርያ ያላቸው እንደነበሩና በቅርቡ ሥልጣኑ በሚያበቃው ፓርላማ/ቡንደስታኽም ከ 709 የሕግ አውጪዎች 58 ማለትም 8.2 በመቶ የሚሆኑት ብቻ የውጭ ዜጋ መሠረት ያላቸው ጀርመናውያን መሆናቸውን ጠቅሷል። በነገራችን ላይ በዘንድሮው ምርጫ የመራጩ ሕዝብና ከውጭ ዜጎች የሚወለዱ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ብቻ ሳይሆን የኅብረተሰቡን ጥያቄ እና ፍላጎት ለሟሟላት እንዲረዳ የፓርላማው ወንበር ቁጥርም ወደ 735 ከፍ ብሏል። የዕለቱ የጀርመን እና አውሮጳ መሰናዶ በጀርመን ፖለቲካ የውጭ ዜጎችን ተሳትፎ ይቃኛል።

Deutschland BTW 2021 Armand Zorn SPD
ምስል Sebastian Gollnow/dpa/picture-alliance

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ