1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉ በጀርመን መወገዙ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2010

በተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተካሄዱ ተቃዉሞዎች ፀረ ሴማዊ መፈክሮች መሰማታቸውን የጀርመን መንግሥት አውግዟል።

https://p.dw.com/p/2pEuG
Symbolbild brennende Israel-Fahne
ምስል picture alliance/AP Photo/P. Karadjias

በጀርመን የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉ መወገዙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእየሩሳሌም የእሥራኤል ዋና ከተማነት እውቅና መስጠታቸውን በመቃወም በርሊንን ጨምሮ በተለያዩ የጀርመን ከተሞች በተካሄዱ ተቃዉሞዎች ላይ ፀረ ሴማዊ መፈክሮች መሰማታቸውን የጀርመን መንግሥት አውግዟል። በነዚሁ ሰልፎች የእስራኤል ባንዲራ መቃጠሉንም አሳፋሪ ሲል ኮንኗል። የዶቼቬለ ዋና አዘጋጅ አኒስ ፖል ድርጊቱ ሀሳብን በነጻ ከመግለፅ እና ከዴሞክራሲ መብቶች ጋር የማይገናኝ ነው ስትል በጉዳዩ ላይ በጻፈችው ሀተታ ገልጻለች። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ያቀርበዋል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ