1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጉራፈርዳ የተካሄደዉ ባህላዊ እርቀ ሰላም እና ዉዝግቡ 

ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2014

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በአካባቢያቸው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል የተባለ የባህላዊ እርቀ ሠላም ሥነ-ስርዓት ተካሄደ። ይሁንና እርቀ ሰላሙ የሕግ ድጋፍ ያስፈልገዋል፤ መንግስትም ህግ መስከበሩ ላይ ሊበረታ ይገባል ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/429l5
Äthiopien Gura Ferda Woreda  SNNPR
ምስል Bench Sheko Zone government communication office

«እርቀ ሰላሙ የሕግ ድጋፍ ያስፈልገዋል» ነዋሪዎች

በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በአካባቢያቸው ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል የተባለ የባህላዊ እርቀ ሠላም ሥነ-ስርዓት ተካሄደ።

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የባህላዊ እርቀ ሠላም ሥነ-ስርዓት በአካባቢውን ሰፍኖ የቆየውን ሞትና መፈናቃል ለማስቀረት ያስችላል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የወረዳው ተፈናቃዮች በበኩላቸው እርቀ ሠላም መካሄዱ መልካም መሆኑን በመጥቀስ ተመሳሳይ ክስተቶች እንዳይደርሱ እርቀ ሰላሙ የሕግ ድጋፍ ያስፈልገዋል፤ መንግስትም ህግ መስከበሩ ላይ ሊበረታ ይገባል ብለዋል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ