1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በግሪክ ክስረት እና የጀርመን ፖለቲከኞች ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ መስከረም 2 2004

የጀርመንዋ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል መንግስታቸዉ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰጣት ግሪክ ሙሉ በሙሉ ከስራለች የሚለዉን ሃሳብ ዉድቅ አደረጉ።

https://p.dw.com/p/RlRv
ምስል picture-alliance/dpa

ቻንስለርዋ ዛሪ ለአንድ ራድዮ ጣብያ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ግሪክን ጨምሮ ኪሳራ የገጠማቸዉ የይሮ ሸርፍ ተጠቃሚ አገራት የገጠማቸዉ ችግር አልበቃ ብሎ ችግሩን የሚያባብስ መላምት መሰንዘር ተገቢ አይደለም። የሜርክል ተጣማሪ መንግስት አባል የሆነዉ የነጻ ዲሞክራቶች ፓርቲ በጀርመነኛ ምህጻሩ የ FDP ሊቀመንበር እና የአገሪቱ የኢኮነሚ ሚኒስቴር ፊሊፕ ሮስለር ግሪክ ሙሉ በሙሉ ከስራለች የሚል አስተያየት ሰጥተዉ ነበር። ሜርክል ሮስለርን በስም ባይጠቅሱም አስተያየታቸዉን ግን ነቅፈዋል።
«አሁን በግልፅ እንደሚታየኝ ግሪክ የቤት ሥራዋን መሥራት ያለባት አሁን ነው ። እንደሚመስለኝ ለግሪክ የሚበጅ ነገር ማድረግ የምንችለው የሆነ ያልሆነውን ማሰቡን ትተን ስናረታታት ያለባትን ግዴታ ተግባራዊ እንድታደርግ ስናግዛት ነው!
መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በሌሎች የይሮ ተጠቃሚ አገራት የግሪክ አይነት ችግር እንዳይከሰት በሙሉ አቅማችን እንጥራለን በማለትም ተናግረዋል። የግሪክ መንግስት ምጣኔ ሃብታዊ ታህድሶ ለማድረግ የገባዉን ቃል አላከበረም የሚል ወቀሳ እየተሰነዘረበት ነዉ። ጀርመንን የመሳሰሉ ለግሪክ ከፍተኛ ድጋፍ የሚሰጡ አገራት ፖለቲከኞች በግሪክ ሁኔታ ቅር መሰኘታቸዉን እየገለጹ ነዉ።
አዲስ በደረሰ ዜና ግሪክ ከገባችበት የምጣኔ ሃብት ድቀት ለማገገም 20.000ያህል የመንግስት ሰራተኞችን ከስራ ለማባረር እቅድ ላይ መሆንዋ ተገልጾአል።

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ