1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጎንደር የተቀሰቀሰዉ ግጭት

Merga Yonas Bulaረቡዕ፣ ሐምሌ 6 2008

በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና በታጠቁ የፌዴራል ሃይል መካከል ትላንትናዉ ጠዋት በተፈጠረዉ ግጭት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉ እና ንብረትም መዉደሙ ዘገባዎች ያሳያሉ።

https://p.dw.com/p/1JOND
Karte Äthiopien englisch

[No title]

ለግጭቱ መነሻ የሆነዉ ለወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ በኮሚቴ ተወክለዉ ሲከታተሉ የነበሩት አራት ሰዎች በፌዴራል ኃይል በመተሰራቸዉና ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የተባሉትን አምስተኛዉን የኮሚቴ አባል አልታሰርም በማለታቸዉ መሆኑን ለጉደዩ ቅርበት ያላቸዉ ይናገራሉ። ይሁን እንጅ የኢትዮጲያ መንግስት ሚድያዎች በሚያወጡዋቸዉ ዘገባዎች ግለሰቡ «በኤርትራ ከመሸጉ ፀረ-ሰላም ኃይሎች መመሪያ በመቀበል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደርና በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞኖች ሰላማዊ ሰዎችን የገደሉና ዝርፊያ የፈፀሙ» ሲል ወንጅሏቸዋል።


በየግዜዉ መርጃ እየተቀበልኩ ነዉ የሚሉት በአማራ ክልል የኮሙኒኬሸን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የተከሰተዉን አረጋግጦ ታሰሩ የተባሉት ግለሰቦች የዋልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ ማኅበረሰቡን ወክለዉ ሲከታተሉ ነበር ለሚለዉ ያላቸዉ መረጃ የተለየ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የአካባቢዉ ነዋሪዎች የታዘቡት ካለ አስተያየታቸዉን እንዲሰጡን ጠይቀን ነበር። የጎንደር ተዋለጅ ነኝ ያሉንና ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት ግለሰብ ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት የወልቃይ ጠገዴን ጉዳይ መንግሥት ቀልል አድርጎ አይቶታል፣ ግለሰቦቹን «ፀረ-ሰላም» ናቸዉ ብሎ ስም መለጠፍ ነገሮችን አባብሶታል ይላሉ።

ጉዳዩን ለመፍታት መንግስት በጠረጴዛ ዙርያ ከማኅበረሰቡ ጋር በዉይይት መፍታት አለበት እንጅ አፈና፣ ግድያ ወይም ዛቻ መፍቴ አይሆንም ሲሉ እኝሁ አስተያየት ሰጭ አክሎዋል። ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆናቸዉን የነገሩን በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት የሕግ ባለሙያዉ አቶ ከበደ ኃይለማርያም የወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ ትክክል ነዉ ይላሉ።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ