በጠ/ሚ መለስ ሞትና የብራስልስ አስተያየት15 ነሐሴ 2004ማክሰኞ፣ ነሐሴ 15 2004ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ብራስልስ ቤልጂግ በሚገኝ ሆስፒታል ዉስጥ ሲታከሙ መቆየታቸዉ ሲነገር ነዉ የሰነበተዉ። ሆኖም እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ሆስፒታሉ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም የቤልጅግ መንግስት ይህን በትክክል አልገለፁም።https://p.dw.com/p/15tu1ምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያ ተጠይቀዉም አላመኑምም ነበር። ዛሬ ግን ብራስልስ ዉስጥ ሲታከሙ እንደቆዩ የሚገልፁ ዘገባዎች ወጥተዋል። የአዉሮጳዉ ኅብረትም በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማዉን ሀዘን ገልጿል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ከኅብረቱና ጠ/ሚኒስትሩ ሲታከሙበት ነበር ከተባለዉ ሀኪም ቤት እንዲሁም ከሌሎች ወገኖች ያሰባሰበዉን አስተያየት ልኮልናል። ገበያዉ ንጉሤ ነጋሽ መሐመድ