1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፀሀይ የምትሰራ አይሮፕላን የሙከራ በረራ

ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2003

ባለፈው ሳምንት አርብ በፀሀይ ሀይል ብቻ የምትንቀሳቀሰው አይሮፕላን በአውሮፓ የሙከራ በረራዋን በሚገባ ተወጥታለች።

https://p.dw.com/p/RObv
André Borschbergምስል Solar Impulse/Jean Revillard/Rezo.ch

የሁለት ሲውዘርላንዳዊያን የስራ ውጤት የሆነችው አይሮፕላን፤ ከ ሲውዘርላንድ ተነስታ ከ 12 ሰዕት 59 ደቂቃዎች በኋላ ብራስልስ ላይ ስታርፍ በጠቅላላ የተጓዘችው 600 ኪሎ ሜትር ገደማ ነበር። አይሮፕላኗ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከሲውዘርላን የአየር ሀይል ተነስታ፤ በፈረንሳይና ሉክሱንበርግ ላይ በራ፤ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ግድም ነበር በፖሊስ ሄሊኮፕተር ታጅባ ቤልጄም መዲና ብራስልስ ያረፈችው። ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት፤ የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ክፍል ኃላፊ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያም አድርገዋል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሠ