1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቡርቃና ጀርመናውያን

ማክሰኞ፣ ግንቦት 10 2002

የፈረንሳይ ፓርላማ አንዳንድ ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱትን መላ ሰውነትን የሚሸፍነውን ቡርቃን የሚያወግዝ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል ። የቤልጂግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤትም ቡርቃ በህግ እንዲታገድ በቅርቡ ተስማምቷል ።

https://p.dw.com/p/NREd
ምስል picture-alliance/dpa

ይህ በቤልጂግ ተጀምሮ በፈረንሳይ የቀጠለው በቡርቃ ላይ የተወሰደ ጥብቅ ዕርምጃ በሌሎች የአውሮፓ ሐገራትም ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል የብዙዎች ግምት ነው ። ጉዳዩ እዚህ ጀርመንም በየምክንያቱም ማነጋገሩ አልቀረም ። የቡርቃ መታገድ ደጋፊዎች አለባበሱ ከባህላዊ እሴቶቻችን ውጭ ከመሆኑም በላይ የሴቶች ጭቆና ምልክት ነው በማለት ሴቶች ፊታቸውን ሸፍነው እንዲሄዱ መፈቀድ የለበትም ይላሉ ። በሌላ ወገን ደግሞ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እናራምዳለን በሚሉ ሐገራት የሰዎች አለባበስ ላይ ገደብ መጣሉ ተገቢ አይደለም ፤ እገዳው የአለባበስ ነፃነትን ይጋፋል ሲሉ የሚከራከሩም አሉ ። ክርክሩ በዚህ መልኩ በቀጠለበት ሁኔታ ጀርመናውያን ስለ ቡርቃ ምን አስተያየት እንዳላቸው ለመረዳት የዶይቼቬለ ራድዮ የአረብኛ ቋንቋ ክፍል ባልደረባ ሻምስ አያሪሽ ቡርቃ ለብሳ በኮሎኝ ከተማ ተዘዋውራ ነበር ። በዛሬው ዝግጅታችን ልምድዋን ታካፍለናለች ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ