1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ቢያንስ አንድ የውሃ ጉድጓድ እናስቆፍራለን»

ዓርብ፣ ኅዳር 21 2005

አብዛኞቹ በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው። ከትምህርታቸው ጎን በንፁህ ውሃ አቅርቦት ላይ ይሰራሉ።

https://p.dw.com/p/16oKo
***Achtung: Nur zur mit HFDW abgesprochenen Berichterstattung verwenden!*** Wasserprojekt für die Dorfbewohner in Mekele, unterstützt von Studenten. *** Bild von Help For A Drop Of Water, eingestellt im November 2012
ምስል HFDW
***Achtung: Nur zur mit HFDW abgesprochenen Berichterstattung verwenden!*** Dorfbewohner freuen sich auf die Fertigstellung ihres Brunnens. *** Bild von Help For A Drop Of Water, eingestellt im November 2012
የውሃ ጉድጒድ የተቆፈረላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች በደስታ ሲጨፍሩምስል HFDW
***Achtung: Nur zur mit HFDW abgesprochenen Berichterstattung verwenden!*** Wasserprojekt für die Dorfbewohner in Mekele, unterstützt von Studenten. *** Bild von Help For A Drop Of Water, eingestellt im November 2012
ምስል HFDW

ሐርሜላ ወንድሙ ተወልዳ ያደገችው ሐረር ከተማ ነው። ለትምህርት ወደ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በሄደችበት ወቅት ስላነቃቃችው እና በትንሹ ተጀምሮ ዛሬ የዕለት ውሎዋ ስለሆነው ስራ ታጫውተናለች። ወጣቷ በአሁኑ ሰዓት «ሄልፕ ፎር ኤ ድሮፕ ኦፍ ወተር» በመባል የሚጠራው ማህበር ፕሬዚዳንት ናት። ይህንን ማህበር ሐርሜላ እና የትምህርት ቤት ባልደረቦቿ ናቸው በህብረት ያቋቋሙት- ስለ አጀማመሩ አጫውታናለች።

በአንድ የውሃ ጉድጓድ ማስቆፈር የተጀመረው ፕሮጀክት አድጎ ማህበሩ እስካሁን ሶስት ጉድጓዶችን አስመርቋል። ከሁለት ወር በኋላ የሚመረቁ ደግሞ ሌሎች አራት ጉድጓዶች እንዳሉ ሐርሜላ ገልፃልናለች። ማህበሩ በአሁን ሰዓት ከተለያዩ ክልሎች ለትምህርት ወደ መቀሌ ዮንቨርሲቲ በመሄድ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከ 2500 በላይ በጎ ፍቃደኞች አሉት። ከነዚህ በጎ ፍቃደኞች አንዱ እዮኤል ጌታቸው ነው። በመቀሌ ዮኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት ነው ማህበሩን የተቀላቀለው። በአሁኑ ሰዓት ትምህርቱን አጠናቆ በአዲስ አበባ ከተማ ይኖራል። ማህበሩን በትርፍ ጊዜው መደገፉን ግን እንዳላቋረጠ ነግሮናል። ለምን እና እንዴት አባል ሆነ? መልስ ሰጥቶናል።
ሌላዋ ፌቨን ታደሰ ናት። በአሁኑ ሰዓት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ አመት ሲቪል ኢንጂነሪንግ ተማሪ ናት። እሷም ያየችው አሳምኗት ነው አባል የሆነችው። በተማሪ አቅሟ ለማህበሩ ያላትን አስተዋፅዎ ገልጻልናለች።

የቀድሞ የመቀሌ ዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስላቋቋሙት «ሄልፕ ፎር ኤ ድሮፕ ኦፍ ወተር» በመባል ስለሚታወቀው ማህበር የበለጠ ከድምፅ ዘገባው ታገኛላችሁ።

ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ