1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህል ሙዚቃ እና ሙዚቀኛ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 19 2004

የባህል ሙዚቃን በማዜምዋ ተወዳጅነትን ያተረፈችዉ የዝና ነጋሽ የእለቱ ዝግጅታችን እንግዳችን አድርገን ይዘናታል።

https://p.dw.com/p/13b3K
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

እዚህ በአዉሮጳ አገራት በሚገኙ በበርካታ መድረኮች የኢትዮጵያን የባህል ሙዚቃ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የባህል አልባስትን በማድረግዋ የባህል ዉዝዋዜን በማሳየትዋ የባህላዊ ሙዚቃ አምባሳደር መሆንዋ ይነገርላታል። ሰቆጣን፣ በትዝታ፣ ዜማዋ፣ ሰቆጣ በተሰኝዉ ዘፈንዋ ኢትዮጽጵያዉያን ብቻ ሳይሆን ባህሉን የማያዉቁትን ቋንቋዉን የማይናገሩትን ጭምር ልብ ትሰርቃለች። ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት የቀሩት የአዉሮጳዉያኑ2011 ዓ.ም በዚህ በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም ይህንኑ የጎርጎረሳዉያን ዓመት በሰላም ሸኝተዉ አዲሱን ዓመተ ምህረት ሊቀበሉ በዝግጅት ላይ ናቸዉ። በአዉሮጳ አገራት የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ም ግብቤት መድረኮችም ኢትዮጵያዉያን ባህላዊ ምግብ አልባሳትን ዉዝዋዜን በማሳየት አዲሱን የጎርጎረሳዉያን ዓመት እና የገና በአልን የሚያከብሩት ጥቂቶች አይደሉም። በብሪታንያ ለንደን ከተማ ነዋሪ ከሆነች አስራሶስተኛ አመትዋን የያዘችዉ የባህል ሙዚቀኛ የዝና ነጋሽ በትልልቅ በአላት ግዜ ወደየተለያዩ የአዉሮጳ አገራት መድረኮች ሙዚቃዋን ታቀርባለች። ሙሉዉንቅንብርያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ