1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባለስልጣናት ምስክርነት እንዳይሰጡ ፍ/ቤት ወሰነ

ሐሙስ፣ ጥር 3 2010

የመንግስት ባለስልጣናት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች በነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ በፀረ/ሽብር ሕግ በተከሰሱት ችሎት ላይ ለመከላከያ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የተከሳሶች ጠበቃ ያቀረቡትን ጥያቄ  የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል።

https://p.dw.com/p/2qhuc
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

የመንግስት ባለስልጣናት  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች በነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ በፀረ/ሽብር ሕግ በተከሰሱት ችሎት ላይ ለመከላከያ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የተከሳሶች ጠበቃ ያቀረቡትን ጥያቄ  የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ውሎው «በሙሉ ድምፅ» ውድቅ አድርጎታል። ውሳኔው እንደተሰማ  ተከሳሾች ተቃውሟቸውን የትግል መዝሙር በመዘመር በማሰማታቸው ፍርድ ቤት ደፍራችኋላ በሚል በተከሳሾች ላይ ከሶስት ወር እስከ ስድስት ወር የእስራት ቅጣት እንደተላለፈባቸው እና  ለጥር 10 ቀን 2010 ዓ ም ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠ በፍርድ ቤቱ ተግኝቶ የነበረዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር የላከው ዘገባ ያመለክታል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ልደት አበበ