1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባለፈዉ ዓርብ የታሠሩት ሙስሊሞች ጉዳይ

ማክሰኞ፣ የካቲት 26 2005

የታሳራዊዎቹ ቤተ-ሠቦች እና የአይን ምሥክሮች እንዳስታወቁት ፖሊስ በተለይ ከአንዋር መስጊድ አካባቢ እየለቀመ ካሠራቸዉ ወጣቶች መሐል ከአሥር የሚበልጡት ሴቶች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/17qtC
ምስል picture alliance/dpa

የኢትዮጵያ መንግሥት ሐይማኖታዊ ነፃነታቸዉ እንዲከበር ከጠየቁና ሕገ-ወጥ የቤት ለቤት አሰሳ መደረጉን ከተቃወሙ የአዲስ አበባ ሙስሊሞች መካካል ከሃያ-የሚበልጡ ወጣቶችን ባለፈዉ አርብ አስሯል።የታሳራዊዎቹ ቤተ-ሠቦች እና የአይን ምሥክሮች እንዳስታወቁት ፖሊስ በተለይ ከአንዋር መስጊድ አካባቢ እየለቀመ ካሠራቸዉ ወጣቶች መሐል ከአሥር የሚበልጡት ሴቶች ናቸዉ።ወጣቶቹ በብዛት የታሠሩበት ፖሊስ ጣቢያ፥ የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዦችም ሆኑ የኮሚኒኬሽን መሥሪያ ቤት ባለሥልጣናት ወጣቶቹ የታሠሩበትን ምክንያት፥ ብዛታቸዉንና የሚገኙበትን ሥፍራና ሁኔታ ለመግለፅ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም እስካሁን ፍቃደኞች አይደሉም።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

------------------------------------------------------------

አድማጮች አሁን በደረሰን ጥቆማ መሠረት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ደ ኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ጉዳዩን አጣርተዉ ነገ መግለጫ እንደሚሰጡ አስታዉቀዋል። መግለጫዉ እንደደረሰን እንደምናቀርብ እንገልፃለን።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ