1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባልደራስ በአዲስ አበባ የተደረገውን ምርጫ ውጤት እንደማይቀበለው ገለፀ 

ዓርብ፣ ሐምሌ 23 2013

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምርጫው በቅድመ ምርጫ ፣ በሂደቱ እና በድምፅ መስጫው ዕለት የነበሩ ሁነቶችን የሚዳስሱ አለም አቀፍ የምርጫ መመዘኛ መስፈርቶችን የሟያሟላ በመሆኑ አልቀበለውም ብሏል። ፓርቲው የድጋሚ ምርጫ ጥያቄ ማንሳቱንና በአዲስ አበባ ካሉት 23 የምርጫ ክልሎች መካከል በ21ዱ ላይ ክስ መመስረቱን ይፋ አድርጓል።

https://p.dw.com/p/3yKn3
Äthiopien Addis Ababa | Pressekonferenz | Balderas
ምስል Solomon Muche/DW

ባልደራስ በአዲስ አበባ የተደረገውን ምርጫ ውጤት እንደማይቀበለው ገለፀ 

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ምርጫው በቅድመ ምርጫ ፣ በሂደቱ እና በድምፅ መስጫው ዕለት የነበሩ ሁነቶችን የሚዳስሱ አለም አቀፍ የምርጫ መመዘኛ መስፈርቶችን የሟያሟላ በመሆኑ አልቀበለውም ብሏል።
ፓርቲው በ6ኛው አገራዊ ምርጫ የአዲስ አበባ ምርጫ እና ድህረ ምርጫ ሂደትን በተመለከተ የግምገማ ውጤቱን ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በጽ/ቤቱ ሲያሳውቅ የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ " ምርጫውን ብልጽግና ፓርቲ መቶ በመቶ ማሸነፍ እንዲችል ተደርጎ ተጠልፏል። ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሓዊ ምርጫ እንዳይደረግ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአጋዥነት ብልጽግና ፓርቲ ደግሞ በዋናነት ምርጫውን ጠልፈውታል" ብለዋል። 

ፓርቲው ከዚህ መነሻ የድጋሚ ምርጫ ጥያቄ ማንሳቱንና በአዲስ አበባ ካሉት 23 የምርጫ ክልሎች መካከል በ21ዱ ላይ ክስ መመስረቱን አሳውቆ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እየተከታተለ መሆኑንም ገልጿል።

ኢትዮጵያ የምትከተለው የምርጫ ሥርዓት አብላጫ ድምፅ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት መንግሥት መመሥረትን የሚያስችል በመሆኑ እና የምርጫ ሕጉ ስለማይፈቅድ እንጂ ባልደራስ በሥራ አስፈፃሚው ውስጥ ውክልና ማግኘት የሚያስችል ድምፅ አግኝቶ እንደነበር ፣ በተወዳደረበት አዲስ አበባ ከተማ በሁለተኛ ደረጃ የመራጭ ድምፅ ያገኘ ፓርቲ መሆኑም ተነግሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ ለመራጭነት የተመዘገበው ሰው ቁጥር ቀደም ብሎ 1.4 ሚሊዮን እንደነበር በምርጫ ቦርድ ከተገለፀ በኋላ ውጤት የተበሰረበት ዕለት የመራጩ ቁጥር 1.8 እንደነበር መገለፁ የፖለቲካ ሸፍጥ ስለመኖሩ ማሳያ ነውም ብሏል ፓርቲው። 
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሰላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥል ተናግራል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ ሰዎችን አዲስ በሚዋቀረው መንግሥት እንደሚያስገቡ መናገራቸውን በተመለከተ የፓርቲውን አቋም ተጠይቀው አቶ ጌታነህ ባልቻ ሲመልሱ "እኛ ሕዝብ የሰጠንን እንጂ ፓርቲ የሚሰጠንን ውክልና አንቀበልም" ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሰ