1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባልደራስ የጋራ መኖሪያ ቤት ያልደረሳቸውን መመዝገብ ጀመረ

ሰኞ፣ ሰኔ 1 2012

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ፓርቲ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ለሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝግበው ገንዘብ የቆጠቡ ነገር ግን ያልደረሳቸው ነዋሪዎችን መመዝገብ ጀመረ። የፓርቲው ሊቀ-መንበር እስክንድር ነጋ "የምርጫ ሰራዊት" ለመገንባት ምዝገባው እንደሚካሔድ ተናግረዋል። 

https://p.dw.com/p/3dRp0
Äthiopien Kaliti Gefängnis
ምስል Befekadu Hailu

ባልደራስ የጋራ መኖሪያ ቤት ያልደረሳቸውን መመዝገብ ጀመረ

እስክንድር ነጋ የሚመራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ፓርቲ ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ለሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝግበው ገንዘብ የቆጠቡ ነገር ግን ያልደረሳቸው ነዋሪዎችን መመዝገብ ጀመረ። ምዝገባው ሲካሔድ የዶይቼ ቬለው ሰለሞን ሙጬ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የሚጠበቅባቸውን የገንዘብ መጠን ቢቆጥቡም የመኖሪያ ቤት እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል። የፓርቲው ሊቀ-መንበር እስክንድር ነጋ "የምርጫ ሰራዊት" ለመገንባት ምዝገባው እንደሚካሔድ ተናግረዋል። 
ሰለሞን ሙጬ ተጨማሪ ዘገባ አለው

ሰለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ