1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባራክ ኦባማና የምጣኔ ሀብት መደጎሚያ ዕቅዳቸው

ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2001

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የአሜሪካን የህግ መወሰኛ ምክርቤት አባላት የምጣኔ ሀብት መደጎሚያ ዕቅድን በአስቸኳይ ካላፀደቁ ሀገሪቷ የባሰ ቀውስ ውስጥ እንደምትገባ አስጠነቀቁ ።

https://p.dw.com/p/Gr6Y
ምስል AP

ኦባማ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስገነዘቡት ዋነኛ ግቡ አሜሪካውያንን መልሶ የስራ ባለቤት ማድረግ የሆነው የምጣኔ ሀብት መደጎሚያ ዕቅድ ተግባራዊ ሲሆን አራት ሚሊዮን ስራ ይፈጥራል ። ፕሬዝዳንቱ የሀገሪቱ የምጣኔ ሀብትን መዋቅር ወደ ነበረበት ፣ለመመለስ ገበያውን ለማረጋጋት እና ህብረተሰቡም በመዋቅሩ ላይ ዕምነት እንዲኖረው ግልፅነት እና ተጠያቂነትን ያካተቱ የአሰራር ስልቶች እንደሚዘረጉም ጠቁመዋል ። ከዋሽንግተን ዲሲ አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ አለው