1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባዶ እግሯሟ የሙዚቃ አምባሳደር

ረቡዕ፣ ጥር 23 2004

በባዶ እግሯ የአለምን የሙዚቃ መድረክ በልዮ ዜማዋ በማንቆርቆሯ በባዶ እግር የምታዜማዋ የሙዚቃ እመቤት የሚል መጣርያ የተሰጣት አፍሪቃዊትዋ ሲሳሪያ ኤቮራ ባለፈዉ ሳምንት ቅዳሜ በ 70 አመትዋ ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

https://p.dw.com/p/13Xzu
ምስል AP

የሙዚቃ ድግስዋን ስታሳይ በመድረክ ላይ  የምትወጣዉ በባዶ እግሯ በመሆኑ ይታወቃል። ጫማ እንደማትወድ እና ገበያ ስትሄድ ሁሉ በባዶ እግሯ እንደሆነም ገልጻለች።  ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ዋላችሁ የሲሳሪያ ኤቮራ ሙዚቃ እንደዚህ እንዳደመጣችሁት የምታዜምበት የፖርቱጋል ቋንቋ ፍችዉ ከቋንቋዉ ተናጋሪዎች ሌላ ባይገባም ዜማዉ ትዝታን ሃዘንን ፍቅርን ብቸኘትን ናፍቆትን እንዲህ እንዳደመጣችሁት ያሰንቃል ። ምዕራብ አፍሪቃዊትዋ የሙዚቃ ንግስት በመባል የምትታወቀዋ የካፕቬርዴዋ ሲሳሪያ ኤቮራ የአለምን የሙዚቃ መድረክ ለመጀመርያ ግዜ በሰማንያዎቹ አመተ ምህረት በአርባ ሰባተኛ አመትዋ ነዉ አሃዱ ብላ የተዋወቀችዉ። ወደዚሁ ግዙፍ መድረክ ከመቅረብዋ በፊት ግን ድህነት የአልኮል መጥጥ ችግር አንዱ ችግሯ እንደነበር ይነገርላታል። ያም ሆኖ በትዝታን መሰል ዜማዎችዋ በአገርዋ ያለዉን ችግረኛ ማህበረሰብ ተስፋ በመስጠት እና በቻለችዉ ሁሉ ችግረኛን በመርዳትዋ ትታወቃለች። ስለ ከያኒዋ ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘናል! ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ