1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤተ-እስራኤላዉያን እስራኤል ገቡ

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2011

82 ኢትዮጵያዉያን-የሁዳዉያን ወይም ቤተ-እስራኤላዉያን ትናንት ከኢትዮጵያ እስራኤል ገቡ።ኢትዮጵያዉያን የሁዳዉያኑ እስራኤል የገቡት ከበርካታ ዓመታት ክርክርና ጥበቃ በኋላ ነዉ።ሌሎች 8 ሺሕ ኢትዮጵያዉያን የሁዳዉያን እስራኤል ለመግባት አሁንም በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/3Cm0J
Israel Jerusalem
ምስል picture alliance/AP Photo/O. Balilty

ወደ መቶ የሚሆኑት ናቸዉ የእስራኤልን ምድር የረገጡት

እስራኤል ከኢትዮጵያ የተጓዙትን ቤተ-እስራኤላውያን ሙሉ ለሙሉ እንደ አይሁድ ሳይኾን የአይሁድ ዝርያ ያላቸው አድርጋ እንደምትቆጥራቸው አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል። እስራኤል ቀሪ ቤተ-እስራኤላውያንን ከኢትዮጵያ  ልትወስድ ቃል ብትገባም መዘግየቷ እንዳበሳጫቸው ቤተ-እስራኤላውያኑ እና የመብት ተሟጋቾች ገልጠዋል። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ቤተ-እስራኤላውያን በዘመቻ ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የተወሰዱት ከሰላሳ ዓመታት በፊት ነበር። የእስራኤል መንግስት 82ቱን ሰዎች በዚሕ ወቅት እስራኤል እንዲገቡ መፍቀዱ ከፍትሐዊና ሰብአዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ እድምታ አለዉ የሚል ትችት እየተሰማ ነዉ።በእስራኤል ክነሴት (ምክር ቤት) የሰዉ ኃይል አደረጃጀት የትምሕርትና ሥልጠና አስተባባሪ አቶ ዮናታን ታከለም ትችቱን ይጋራሉ።

 

ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ