1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ መስተዳድር ርምጃ ዉጤት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2008

ቤታቸዉ በመፍረሱ ምክንያት ልጆቻቸዉን በየሥፍራዉ ለመበተን፤ በሽተኛ የቤተ-ሰብ አባል ሳይቀር ሜዳ ላይ ለመዉደቅ ተገድደዋል።ባሁኑ ወቅት እየጠነከረ የመጣዉ የክረምት ዝንብና ቁርም እያሰቃያቸዉ ነዉ

https://p.dw.com/p/1JTFP
Äthiopien - Zerstörte Häuser und deren ehemalige Bewohner in Addis Abeba
ምስል DW/Y. Egziabare

[No title]

የአዲስ አበባ መስተዳድር «በሕግ ወጥ መንገድ የተሠሩ» በሚል ሰበብ መኖሪያ ቤታቸዉን ያፈረሰባቸዉ የከተማይቱ ነዋሪዎች በመጠለያ እጦት እየተሰየቃዩ መሆኑን አስታወቁ። ነፋስ ስልክ-ላፍቶ በተባለዉ አካባቢ የነበረ ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት ቤታቸዉ በመፍረሱ ምክንያት ልጆቻቸዉን በየሥፍራዉ ለመበተን፤ በሽተኛ የቤተ-ሰብ አባል ሳይቀር ሜዳ ላይ ለመዉደቅ ተገድደዋል።ባሁኑ ወቅት እየጠነከረ የመጣዉ የክረምት ዝንብና ቁርም እያሰቃያቸዉ ነዉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ችግረኞቹን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ