1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሩክ የሺጥላ እና ስዕሎቹ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2006

የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ ይባላል። ወጣቱ የሚስላቸው ስዕሎች ብቻ ሳይሆኑ የሚስልበት ሁኔታም ከበርካታ ሰዓሊዎች ለየት ያደርገዋል።

https://p.dw.com/p/1BrgF
Brook Yeshitila Künstler mit Behinderung
ምስል Brook Yeshitila

ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ እስካሁን አንድ በጋራ እና ሶስት ደግሞ የግል አውደ ርዕዮችን ለተመልካች አቅርቧል። ብሩክ የስዕሎቹን ይዘት እና መልዕክት አጫውቶናል።

ከዚህም ሌላ ልደቱን ነገ ያከብራል። ዕለቱ ግን የተወለደበት ቀን አይደለም። ልደቱን አስቀድሞ ማክበር ያስፈለገበት ምክንያት የተወለደበት ቀን ትልቅ ቀዶ ህክምና ስለሚኖረው ነው። ይህ ብቻ አይደለም።

Brook Yeshitila Künstler mit Behinderung
የብሩክ እንደ ጠመኔ፣ እንቁላል እና ሌሎች መገልገያዎችን እየተጠቀመ ይስላል።ምስል Brook Yeshitila

ካለፉት ሰባት አመታት አንስቶ ልደቱን ከጓደኞቹ ጋር ተሰባስቦ ሲያከብር፤ ወጣቱ የሚያከብርበትን ገንዘብ ለሌሎች የሚጠቅሙ ነገሮችን በመግዛት ወይም በማድረግ እንደሚያሳልፍ ገልፆልናል። ያለፈውን ዓመት ለምሳሌ ድሮ ለተማረበት ት/ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መፅሀፍ ሲገዛ፤ ለዚህኛው አመት ደግሞ አዲስ እቅድ አለው። የብዙ ሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ሰዎችን ሰብስቦ ደም እንዲለግሱ ያደርጋል።

ብሩክ ከቀዶ ህክምናው በኋላ አዲስ አውደ ርዕይ ለማሳየት አላማ እንዳለው ነግሮናል። ከዛ በፊት የብሩክን ስዕሎች ለማየት ለምትፈልጉ አድማጮች ድረ ገፁ www.brookyeshitila.comነው።

ከብሩክ የሺጥላ ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ