1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሪታኒያ ከአዉሮጳ ኅብረት ለመዉጣት ወሰነች

ዓርብ፣ ሰኔ 17 2008

የብሪታኒያ ዜጎች ሀገራቸዉ በአዉሮጳ ኅብረት አባልነቷ ትቀጥል አትቀጥል በሚል በሕዝበ ዉሳኔ ከኅብረቱ ለመዉጣት ወሰኑ። ይህን ተከትሎ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሚሩን ስልጣናቸዉን እንደሚለቁ ይፋ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/1JC34
Großbritannien EU-Referendum Brexit Nigel Farage
ምስል Reuters/T. Melville

[No title]

በዚህ አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የሀገሪቱ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የንግዱ ማኅበረሰብ እና ሌሎችም ተቋማት በየአቅጣጫዉ ሲወያዩ ሲከራከሩበት ሰንብተዉ፤ ሲያካሂዱት የነበረዉ በአባልነት እንቀጥል አንቀጥል ዘመቻ ትናንት ነበር ያጠናቀቁት። ትናንት ምሽት ሊከተል የሚችለዉን ዉጤት ምንነት የሚጠቁም ዘገባ ባይወጣም የድምፅ አሰጣጡ ሂደት እየተካሄደ መሆኑ ተነግሮ ነበር። በጉዳዩ ላይ ዉሳኔዉን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ድምፁን በይፋ በመስጠት ለመወሰን የወጣዉ የብሪታንያ ሕዝብ ጥቅሙን ከጉዳቱ በአግባቡ መዝኖ እንዲያከናዉን የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ትናንት ማሳሰባቸዉ ይታወቃል።

ኢፕሶ ሞሪ» ለ«ኢቭኒንግ ስታንዳርድ» ለተባለው ጋዜጣ ያጠናቀረው የሕዝብ አስተያየት መለኪያ መዘርዝር እንዳሳየው፣ ብሪታንያ በአውሮጳ ህብረት ውስጥ ትቆይ የሚለው ቡድን 52% ፣ ትውጣ የሚለው ደግሞ 48% ድምፅ ያለው እንደሚመስል ሁሉ ተዘግቦ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ፣ ትናንት በደቡብ ምዕራብ ለንደን በጣለው ብርቱ ዝናብ የተነሳ በርካታ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋት እና ወደሌላ ቦታ መዛወር ነበረባቸው።

ድልነሳ ጌታነህ/አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ