1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተስፋ አስቆራጩ የኃይል መቆራረጥ

ዓርብ፣ መጋቢት 15 2009

የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት አቅርቦት እና የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ይቀርብበታል። የኃይል አቅርቦቱ በተደጋጋሚ ይቆራረጣል ሲሉ ቅሬታ የሚያቀርቡ ኢትዮጵያውያን አገልግሎቱ የሚታዩበት ችግሮች በቅርብ ጊዜ መፍትሔ ለማግኘቱ ጥርጣሬ አላቸው።

https://p.dw.com/p/2Zv59
Äthiopien Gide III Staudamm
ምስል Getty Images/AFP

Power outage affects day to day life in Ethiopia - MP3-Stereo

ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ኬንያ፤ሱዳን እና ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል ትሸጣለች። አዳዲስ የኃይል ማመንጫዎች በመገንባት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ እነ ታንዛኒያ እና የመንን ከደንበኞቿ መካከል ልታደርግም አቅዳለች። የኃይል አቅርቦቱም ሆነ የአገልግሎት አቀራረቡ ግን በኢትዮጵያውያን ዘንድ ወቀሳ ይበዛበታል። የሆለታ፤ሎጊያ ወልዲያ ከተሞች ነዋሪዎች እንደሚሉት የኃይል መቆራረጡ በለት ተለት ሕይወታቸው ላይ ጫና አሳድሯል። 

በዋትስ አፕ አስተያየታቸውን ያደረሱ አድማጮቻችን እንደሚሉት ጅማ አካባቢ የመቆራረጥ ችግር የተለመደ ነው፤በአዳማ ከተማ ቀበሌ አስራ አራት መብራት በቀን በአማካኝ ሶስት ጊዜ ይጠፋል።  በኃይል መቆራረጥ ሳቢያ ወሎ ውርጌሳ «ሕብረተሰቡ ከፍተኛ ችግር ላይ ነው። በተለይ ወፍጮና ዳቦ ቤት።» የኢትዮጵያ መንግሥት የኃይል አቅርቦቱም ይሁን የአገልግሎት አሰጣጡ ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በተግባር የታየው ግን ዜጎችን አላረካም።

እሸቴ በቀለ

አርያም ተክሌ