1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዉሞና ደጋፊ ሰልፎች በኢራን

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 22 2002

በኢራን የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፎችን ተከትሎ በመላ አገሪቱ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች እየተካሄዱ ነዉ።

https://p.dw.com/p/LHuN
መንግስትን ደጋፊዉ ሰልፍ በአብዮት አደባባይምስል AP

በፖሊስና በሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል በተካሄደ ግጭት ብዙ ሰዉ ከሞተ በኋላ፤ በርካቶችም ከቆሰሉ ወዲህ የኢራን መንግስት የተቃዉሞዉን እንቅስቃሴ በቴህራን ለመቅጨት ደጋፊዎቼ ናቸዉ የሚላቸዉን በሺና በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ እንዲወጡ አዟል። እነሱም ወጥተዉ ሞት ለሙሳቪ የሚለዉን ርግማናቸዉን በተቃዉሞዉ ወገን መሪ፤ እንዲሁም ከጀርባ አሉ ባሏቸዉ ወገኖች ላይ አዉርደዋል።

የዶቼ ቬለዉ ዑልሪሽ ፒክ ከቴህራን ለላከልን ዘገባ ይልማ ኃይለ ሚካኤል ከበርሊን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ