1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዋሚዎችና ምርጫ 2002

ሰኞ፣ ግንቦት 30 2002

4ኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ ከተካሄደ ሁለት ሳምንታት አለፉ።

https://p.dw.com/p/Nk79
ምስል DW

ዛሬም ተቃዋሚዎች በጊዜያዊ የምርጫው ውጤት ላይ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ናቸው። ጊዜያዊ ውጤቱ ከተገለጸ ከሁለት ቀናት በሃላ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የጠየቁት ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኢአድ እና መድረክ፤ ማስረጃዎቻችንን ለምርጫ ቦርድ አቅርበን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው ይላሉ። የመላው ኢትዮዽያ አንድነት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አቶ ማሙሸት አማረ እንደሚሉት እስከ ግንቦት 24/2002 አስራአንድ ሰዓት ድረስ በተሰጠን ቀነ ገደብ መሠረት ባለ 50 ገጽ ማስረጃዎች አጠናቅረን ለምርጫ ቦርድ ሰጥተናል። ምላሽ እየጠበቅን ነው ሲሉ ይገልጻሉ። እስከመቼ ምላሹ እንደሚሰጣቸው ግን አልተነገራቸውም። የ8 ፓርቲዎች ጥምረት የሆነው መድረክም ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ማስረጃዎቹን ለምርጫ ቦርድ አቅርብዋል።